እስክስታ ጭፈራና ዘፈን

እስክስታ ጭፈራና ዘፈን ኢትዮጵያዉያን በበአላት በሰርግ በድግስና አዝማሪዎች በሚዘፍኑባቸው ቦታዎች የሚዘወተሩ መዝናኛዎች ናቸው። አዝማሪዎች በሚያዝናኑበት መጠጥ ቤቶች ይዘፈናል እስኪስታ ይወረዳል ወይም ይጨፈራል።

ዘፋኙ የአማርኛ ዜማዎችን በማሲንቆ በዋሺንት በክራርና በከበሮ እየታጀበ በድምጹ ሲያንያንቆረቁር እስክስታ መችዉ ወም ጨፋሪው የድምጹን ቃና በመከተል እስክስታ ይመታል ወይም ይወዛወዛል። ለዛሬ በጥቂቱ የምንመለከተው የተወዳጁንና የዝነኛዉን የእስክስታ አመታት ስርአትን ነው።

እስክስታ በስርአት ስንመታ ወይም ስንወረድ ሁለቱም እጆቻችን ታጥፈው መሃል ወገብ ወይም በሽንጣችን ላይ በማረፍ የደጋን ቅርጽ ይፈጥራሉ። አዉራ ጣታችን ወደሁዋላ ሲያመለክት አራቱ ጣቶቻችን ደግሞ ፊት ለፍት ባለው ወገባችን ላይ አርፈው መታየት አለባቸው። ጣቶቻችን ከታጠፉ ወይም ወድሁዋል ከተሸጎጡ ጸያፍ እስክስታ ያደርገዋል ወይም አላዋቂነታችንን ያሳብቅብናል።

የእስኪስታ አወራረድ ወይም አመታት እንደ ተወዛዋዡዋ(ው) የእስኪስታ ልምድ የሰዉነት ብቃትና ቅልጥፍና ይለያያል። አልፎ አልፎ ሴቶች እስክስታ ሲመቱ የመቀነታቸዉን ጫፍ (ጥለት) በመበተንና የወፍ ክንፍ በመስራት ወገባቸዉን ይዘው ወይም የመስቀል ቅርጽ በመስራት ሲወዛወዙ ልዩ ዉበትን በመጎናጸፍ አዳማጭን ይማርካሉ። አሁን ባለንበት ዘመን እስኪስታ በኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሚኖርባቸው ውጭ ሃገሮች ሁሉ እየታወቀና እየተወደደ በመሄድ ላይ ነው።

Iskista is unique and very much loved Ethiopian entertaining Amhara Dance. It has become popular with many other people around the world.  To make an appropriate and impressive Amharic iskista both of your hands shall rest at your waist and your thumb shall point towards your back while your four fingers are visible in front of your body. At this time you will create 2 lovely triangles at left and right side of your main body.  The quality, speed and the type of Iskista/movement depends on your staminaability and endurance and the rhythm of music you are listening to. Enjoy Iskista! Love Ethiopia!!

There are few styles of Iskista:

You can move your body left to right and vice versa,

You can shake your shoulders

You can move up and down

You can also shake your whole body . This time both of your hands must point straight down (this variety of Amhara Dance is popular in Gojam).

 

 

ኢትዮጵያዉያን በበአላት በሰርግ በድግስና አዝማሪዎች በሚያዝናኑበት መጠጥ በቶች ይዘፍናሉ እስኪስታ ይወርዳሉ ወይም ይጨፍራሉ።

ኢትዮጵያዉያን በበአላት በሰርግ በድግስና አዝማሪዎች በሚያዝናኑበት መጠጥ በቶች ይዘፍናሉ እስኪስታ ይወርዳሉ ወይም ይጨፍራሉ።
የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.