ብዓዴን የህወሀት ነውረኛ ቡድን እንጂ የአማራ ህዝብ አካል አይደለም!

ብዓዴን የህወሀት ነውረኛ ቡድን እንጂ የአማራ ህዝብ አካል አይደለም! [ክፍል ፫]

በአቻምየለህ ታምሩ

ወያኔ ኢህዴንን ለምን እንደፈጠረውና አዲስ አበባ ከገባ በኋላም

እንደራሴው ብዓዴን በአማራ ህዝብ ላይ ላለፉት ሀያ አራት

አመታት የተፈመውን ግፍና በደል ባለፉት ሁለት ተከታታይ

ክፍሎች አቅርቤያለሁ። በዚህ ክፍል ደግሞ ሰላሳ አምስት

አመታት ሞላኝ የሚለውን የብዓዴን ያልተኖረ ዘመን ዘመነኞች

ስብስብና ተግባር ዳስሰን ጽሁፋችንን እንቋጫለን።

3. ያልተኖረው የብዓዴን ዘመን ዳሰሳ

በክፍል አንድ ጽሁፌ እንደጠቆምሁት ኢህዴንን ወያኔ ሲያቋቁም

ህብረ ብሔራዊ ድርጅት አድርጎ ነው። ወያኔ ኢህዴንን ሲያቋቁም

ከሒርና [ሀረር]፣ ከሲዳሞ፣ ከወለጋ፣ ከደብረ ዘይት፣ ከኮረም፣

ከኤርትራና ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ የኢህአፓ

ታጋዮችን በነአንበርብር አማካኝነት ከኢህአፓ በማስኮብለል ነው።

እናም ኢህዴን የአማራ ብቻ ወኪል ሊሆን አይችልም። ኢህዴን

ከ1973 እስከ 1985 ድረስ «የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ

ንቅናቄ » ወይንም በምህጻረ ቃል ኢህዴን ተብሎ እየተጠራ

ህብረ ብሔራዊ ድርጅት ሆኖ «ሲታገል» እንደኖረ ይታወቃል።

በ1985 ዓመተ ምህረት ደግሞ የአማራን ውልክና ከፕሮፌሰር

አስራት ወልደየስ መአህድ ለመጫረትና መአህድን ለመዋጥ

ወያኔ የብሄረሰብ ድርጅት አደረገው። ዛሬ ግን ብዓዴን እያለን

ያለው ለ35 ዓመታት የአማራን ህዝብ ወክዬ ስለታገልሁ

አማራው 35ኛ አመት ልደቴን ሊያከብርልኝ ይገባል እያለ ነው።

በእውነቱ እንደዚህ አይነቱ ሰንፋጭ ድፍረት አይደለም ለአማራ

ህዝብ ይቅርና ለአልፎ ሂያጅም ይገለማል። ማንም

እንደሚያውቀው ኢህዴን ከ1985 ዓመተ ምህረት በፊት ህብረ

ህሔራዊ ድርጅት ነበር፤ ብዓዴን የሚል የወያኔ አጃቢ

የተፈጠረው በ1985 ዓመተ ምህረት ነው። ታዲያ እንዴት ብሎ

ነው የ23 አመቱ ብዓዴን የ35ኛ አመት ልደቴን አክብሩልኝ እያለ

ያለው? ህብረ ብሔራዊው ኢህዴን የአማራ ተወካይ ነበር

ለማለት ነው? እንዴት ሊሆን ይችላል? የአማራ ህዝብ

ያልኖረውን ዘመኑን ህወሀት ብዓዴን አክብርልኝ ሲለው ከዚህ

በላይ መናቅ የለም ብሎ መነሳት አለበት።

የወያኔ ታማኝ ሞግዚት ሆኖ የኖረው ሳይበቃው ያልተኖረ

ዘመኑን እንዲያከብርለት እያስገደደ ዛሬም ድረስ የቀጠለው

ነውረኛው ብአዴን ላለፉት ሀያ አራት አመታ በኤርትራዊው

መብራህቱ ገብረህይወት [መብርሀቱ በሚል ኤርትራውያን

እናቱና አባቱ ባወጡለት ስም የሚታወቀው አንበርብር በሚል

የበረሀ ስም የሚጠራውና በሚንስትርነት ስሙ ደግሞ በረከት

ሰምኦን ተብሎ የሚታወቀው ግለሰብ እንደሆነ ልብ ይሏል]

እየተዘወረ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለየ ሁኔታ አማራው

ላይ ወያኔ ባልተወለደ አንጀቱ ጫካ በነበረበት ጊዜ የቋጠረውን

ቂምና ጥላቻ ሁሉ ያለ ርህራሔ እንዲያወራርድ ፈቅዷል።

ከመብራህቱ ገብረህይወት የተምታቱ ታሪኮች ዋናው በዘሩ

ኤርትራዊ ሆኖ ሳለ የአማራ ድርጅት መሪ መሆኑ ነው። ይሄ

ከሞራል አንፃር ለአማራ ህዝብ ስድብ ነው። መብራህቱ

ገብረህይወት በህብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነኝ

የሚል ከሆነ ኢትዮጵያንም ቢመራ ጥያቄ ባልተነሳበት ነበር።

ሰው አገሬ የሚለው አገሩ መሆኑ ይታመናልና። የዘር ፖለቲካ

የሚያራምድ ግን የግድ እሱም ዘሩን የሚያቅፍ የፖለቲካ ድርጅት

ወስጥ መግባት ይጠበቅበታል። «አማራ በዘሩ መደራጀት

አለበት» ብሎ ወያኔ ሲያበቃ፣ አማራውን ግን እንዲመሩ

ያስቀመጣቸው አማራ ያልሆኑትንና ከልዩልዩ ዘሮች

ያውጣጣቸውን ምንደኞችና አማራን በመጥላት ክብረ ወሰን

የተቀዳጁ ቅጥረኛ ሰው በላዎችን በመሰብሰብ ነው። ይህም

በመሆኑ የተነሳ ቂም ባዘለ የጥላቻ ክፋት ውስጥ ሆነው

የወያኔን አማራ የማጥፋት ፕሮጄክት ከግብ ለማድረስ አብረውት

ደፋ ቀና እያሉ ከርመዋል።

አዲሱ ለገሰ፣ ህላዬ ዮሴፍ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታደሰ ካሳ፣ ታምራት

ላይኔ፣ ካሳ ተክለብርሀን፣ ወዘተ እንደ መብራህቱ ገብረህይወት

ሁሉ አማራ ያልሆኑና ራሳቸውን ግን የአማራ ህዝብ ወኪል እኔ

ነኝ የሚሉ የአማራ ህዝብ ጠላቶች ናቸው። እነዚህ ሁሉ ወያኔ

ያበጃቸው ፍጡራን አማራን ለማጥፋትና አማራውን በማዳከም

ህወሀትን ለማጠናከር በአማራ ህዝብ አናት ላይ የተቀመጡ

የአማራ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው። የወሎ መሬት ተቆርሶ

ለትግራይ ሲሰጥ፤ የጎንደር መሬት ተገምሶ ለትግራይ ሲታደል፣

ጎጃም ለጉምዝ ተላልፎ ሲሰጥ፤ ሸዋ ለሁለት ሲከፈል፤ አማሮች

እንደ በግ በኦነግና በወያኔ ሲታረዱ እነመብራህቱ

ገብረህይወት፣ አዲሱ ለገሰና ታምራት ላይኔ የሰጡትን ምላሽ

መቼም ልንረሳው አንችልም። አንድ ጊዜ ስለወልቃይትና ሁመራ

እንዲሁም ሰሜን ወሎ ወደ ትግራይ መካለል ተጠይቆ አዲሱ

ለገሰ ሲመልስ እወልከዋለሁ ከሚለው ከአማራ ወገን ሳይሆን

ከትግራይ ወገን ሆኖ «የአማራው ገዢ መደብ ከትግራይ ቆርሶ

የወሰዳቸው መሬቶች ስለነበሩ ነው ወደ ትግራይ የተካለሉት»

ያለው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ዛሬ ፓስተር ሆኛለሁ እያለ

የሚያጭበረብረው ታምራት ላይኔም አማሮች አርባጉጉ፣ ሀረር፣

ወለጋ፣ አርሲ ወዘተ እንደ ፋሲካ ዶሮ ሲታረዱ ካማራ ክልል

ውጭ ያለ አማራ አናቅም ብሎ ተሳልቆባቸዋል።

በክፍል ሁለተ ከቀረበው በተጨማሪ ብዓዴን የአማራ ህዝብ

ጠላትና የህወሀት ሎሌ ስለመሆኑ በርካታ ማስረጃዎች ማቅረብ

ይቻላል። ላለፉት ሀያ አራት አመታት ህወሀት በአማራ ህዝብ

ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ የሚያንገበግባቸው አንዳንድ የድርጅቱ

ወጣት ካድሬዎች ጉርፋርዳ እና ቤንሻንጉል አገራችሁ አይደለም

ተብለው አማሮች ከኖሩበት ቀየ ተፈናቀለው ሜዳ ላይ

የመውደቃቸው ድርጊት የእግር እሳት ሁኖ የሚለበልባቸው ብዙ

ልጆች ነበሩ። በዚህ ሁኔታ ያዘኑና የተቆጡት ወጣቶቹ ብዓዴን

የሚባለው «ድርጅታችን» ቆሜለታለው የሚለው ፍትህ የት አለ፤

እኩልነትስ ከወዴት አለ፤ ኢትዮጵያስ የሁላችን አገር ነች

የምትባለው መገለጫው ምንድ ነው እያሉ የብዓዴንን ስራ

አስፈጻሚ ሞግተዋል። ሆኖም ግን እነዚህ የህዝብ ጥያቄዎች

በአንዳንድ ህሊና ባላቸው የብዓዴን ካድሬዎች መካከል

መመላለስ ሲጀምሩ «ብዓዴን ተዳክሟል» ተብሎ ግምገማ

እንዲያካሂድ በወያኔ ትዕዛ ተላልፎ ነበር። እነአለምነው መኮነን

«በባዶ እግርህ የምትሄድ ድሀ፣ ልጋጋም፣ ሰንፋጭ ንግግር

የምትተፋ፣ ወዘተ» ብሎ ህዝቡ ላይ የተሳለቁበት በወጣት

የብዓዴን አባላት መካከል የህዝቡ ችግር በመነሳቱ «ብዓዴን

ተዳክሟልና ግምገማ ያስፈልገዋል» ብሎ ወያኔ ባዘዘው መሰረት

በተጠራው ስብሰባ ላይ ነበር። ልብ በሉ እንግዲህ! የአማራ

ጉዳይ በብዓዴን ዘንድ የውይይት አጀንዳ ሆኖ ሲቀርብ በህወሀት

ዘንድ ብዓዴን እንደተዳከመ ይቆጠራል። ከጅምሩ ብዓዴን

የተመሰረተው የአማራ ነስፍን አድን የሆነውን መአህድን

ለመዋጥ መሆኑን ከፍ ብለን ተነጋግረናል። ህወሀት ብዓዴንን

ያበጀው የታገለለትን አማራን የማጥፋት ፕሮግራል እንዳሻው

ለማስፈጸም እንቅፋት የሚሆንበትን ለአማራ የሚቆረቆረ ድርጅት

[መአህድ] ውጦ ለማጥፋትና አማራን የማጥፋት ፕሮግራሙን

«በአማራ» ስም በስውርና በዘዴ የሚያስፈጽምለት ድርጅት

ስላስፈለገው ነው። የብዓዴን አላማ የወያኔ ለምዱን አዉልቀን

እርቃኑ አስቀርተን ስናየው አላማው ይህ ነው።

ዛሬ መብራህቱ ገብረህይወት እና አዲሱ ነፃነትን ሳያውቁ

ራሳቸውን የአማራ ነፃ አውጪ አድርገው ራሳቸውን ቢያቀርቡም

እውነታው ግን ሁለቱም የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ የዘለለ

ምንም ሚና የሌላቸው፤ ያልሆኑትን ለመሆን የሚውተረተሩ

የአማራ ህዝብ ገዳዮች ናቸው። ጀርባቸውን ጠንቅቆ ለሚያውቅ

እነዚህ ግለሰቦች ስለ አማራ ህዝብ ነፃነትና ክብር ይሠራሉ ብሎ

ማሰብ የሚቻልበት ሁኔታ የለም። መብራህቱ ገብረህይወትና

አዲሱ ምንም እንኳ ወያኔ ለአላማው ያስቀመጣቸው ፈዳያኖች

ቢሆኑም የአማራ ህዝብ እያኖራቸው ለአማራ ህዝብ ግን ፍቅር

የሌላቸው፤ ከአማራ ህዝብ መሪ ነን እያሉ የማይመሩ፤ እለት

ዕለት በሚፈጥሩት የፍርሃት አረንቋ ውስጥ የሚኖሩ፤ ሠላም

የራቃቸውና ወያኔ የአማራን ህዝብ ለማረድ የሳላቸው ካራዎች

ናቸው። በመሆኑም አማራው ከእነዚህ ግለሰቦች እውነትን ፈልጎ

ማግኘት፤ ነፃነትን ጠይቆ መቀዳጀት፤ ለፍትህ ጥያቄዎች መልስ

ማግኘት አይችልም። የአማራ ህዝብ ከጉራፋርዳ እንዲወጣ

የተደረገበት ምክንያት ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ

«የትምክህተኞች ጥያቄ» ብለው ይሳደባሉ። አያቶቻችን በደምና

አጥንታቸው ያቆዩልንን ድንበር አፍርሳችሁ ለባእዳን ለምን

ትሰጣላችሁ ሲባሉ የጦርነት ናፋቂ ጥያቄ እያሉ ይዘባበታሉ።

እንደምን ሁኖ ከሶስት ሚሊዮን በላይ አማራ ከቁጥሩ ጎድሎ

ተገኘ ሲባሉ የነፍጠኞች ወሬ እያሉ ይሳለቃሉ። አዎን

እነመብራህቱ ገብረህይወት የሚፈልጉት አማሮች ስድባቸውን

ተሸከመው ተዋርደው እንዲጠፉ እንጂ እውነትን፤ ፍትህን እና

እኩልነትን እንዲጠይቁ አይደለም።

የብዓዴን ተልኮ በአማራ ልጆች መካከል የፍትህ፤ የነፃነት እና

የእኩልነት ጥያቄዎች ሥር እየሰደዱ ሲመጡ ጠያቂዎችን

የአማራ ልጆች መግደልና ማሰር በየእለቱ የምንሰማው

«የልማት» ዜናችን ሆኗል። በአማራ ህዝብ መካከል እንደ እሳት

ሰደደ እየተሰራጩ ላሉ የህልውና፣ የፍትህ፤ የነፃነት እና

የእኩልነት እጦት ጥያቄዎች ከህወሃት መራሹ ሞግዚት

[የተቋቋሙት ለነዚህ ህዝባዊ አላማዎች ስላልሆነ] መልስ

ማግኘት የሚቻል አይደለም። ለዚህ ውለታው ነው እንግዲህ

የነመብርህቱ ድርጅት ሰሞኑን «የአማራን ህዝብ ነጻ ላወጣ

የተመሰረትሁበትን ሰላሳ አምስተኛ የልደት ቀኔን ላከብር ነው»

እያለ የአማራን ህዝብ የሚሳደበው። በእውነቱ ይህ ቡድን

ነፃነትን ሳያውቅና ለነጻነት ሳይመሰረት ነፃ አወጣኋችሁ ማለትን

ብቻ የሚያውቅ፤ ወያኔ በእንደራሴነት ለሰጠው ህግ እንኳ

መገዛትን ሳይወድ ስለ ህገ-መንግስት የበላይነት የሚሰብክ፤

ራሱን ከሁሉ በላይ እኔ ነኝ ብሎ ሲያበቃ ስለ እኩልነት ለመስበክ

የማያቅማማ የነውረኞች ስብሰብ ነው። መብራህቱ

ገብረህይወትና አዲሱም የዚህ ነውረኛ ቡድን አካል እንጂ

የአማራ ህዝብ አካል እንዳልሆኑ ባማራ ህዝብ ላይ የፈጸሙትን

ጥፋት በዝርዝር ገልጫለሁ።

ብአዴን ከተመሠረተ በኋላ ከሶስት ሚሊዮን በላይ አማራ

መጥፋቱን በወያኔ ፓርላማ ሪፖርት መደረጉን ሁላችንም

ሰምተናል። ለመሆኑ ከሶስት ሚሊዮን በላይ አማራ የት ጠፋ?

በአገሪቷ ካሉ ብሄረሰቦች መካከል እንደምን ሁኖ የአማራ ቁጥር

ብቻ ሊቀንስ ቻለ? ከአማራ ክልል ወጥተው በሌላ ክልል የሚኖሩ

አማሮች ይሄ አገራችሁ አይደለም፤ ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው

እየተባረሩ ባሉበት ሁኔታ ሶስት ሚሊዮን አማራ ወዴት ሄደ?

ኢትዮጵያ አገራቸው ካልሆነች የአማሮች አገር ወደየት አለች?

ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ተነቅለው ሜዳ ላይ እንዲወድቁ

የተደረጉ አማሮች በደላቸው ምንድ ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች

አማራ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉት መብራህቱ

ገብረህይወትና አዲሱ ለገሰ መልስ አይሰጡም። እነርሱ

የቆሙት በህወሃት«የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት አማራ ነው»

ተብሎ እንዲጠፋ የተወሰነበትን አማራ በሽፋን እንዲጠፋ

ማገዝና በተግባር ማስፈፀም እንጂ ለአማራ ህዝብ ደህንነት

እንዳልሆነ በህዝቡ ላይ ሲፈጽሙት የኖሩት ግፍ፣ ምግባራቸው

እና ግባራቸው ህያው ምስክሮች ናቸው።

ብአዴንን ወያኔ ከፈጠረ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰው

ስነልቦናዊ ግፍ ተነግሮ አያልቅም። የአማራን ቅስም መስበር፤

ትምክህቱን ማስተንፈስ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ማዋረድ፤ ወዘተ

የሚሉት በወያኔ የተሰጣቸው የነመብራህቱ ገብረህይወትና

አጋሮቹ ዋነኛው ጸረ አማራ መፈክሮቻቸው ናቸው። በነዚህ

መፈክሮች መሪነት ከሶስት ሚሊዮን በላይ አማሮች ጠፍተዋል፤

ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለችም ተብለው ከወለጋ፣ ከአርሲ፣

ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ውጡ ተብለው ሜዳ ላይ

ተጥለዋል። ከንግዱ አምባም ሳይቀር ቀስ በቀስ አማሮች

እንዲጠፉ ተደርገው ሥፍራቸውን ለወያኔዎች እንዲለቁ ሁነዋል።

ከፕሮፌሰር አሥራት ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን

አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምልክት እና ጥሩ ምሳሌ የሆኑ

አማሮች ቀስ በቀስ እንዲጠፉ መደረጋቸውን በአይናችን አይተን

በጆሯችን ሰምተናል። ብአዴን የተባለው ድርጅት በአማራ ስም

ቢቋቋምም ቅሉ ዋና ተግባሩ ግን አማሮችን ማዋረድና አማሮች

ላይ የሚደርስባቸውን በደል ሊታደጉ የሚችሉ የአማራ ልጆችም

እንዳይኖሩ ማጥፋት ነው።

ከሁለት አመት በፊት የአማራህ ህዝብ «ትምክህተኞች» እያለ

የሚያስጨርሰው መብራህቱ ገብረህይወት አያሌው ጎበዜን

አስነስቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዲተካው አድርጓል። የአያሌው

መሄድና የገዱ መምጣት ለአማራ ህዝብ ነፃነት እና ክብር

የሚፈይደው አንዳችም ቁም ነገር የለም። አያሌውም ሆነ ገዱ

ለህዝብ ይቅርና ለራሳቸውም ክብር የሌላቸው ደካማ ሎሌዎች

መሆናቸው የታወቀ ነው። ለራሱ ክብር ያለው የህዝብ ወኪል

እወክለዋለው የሚለው ህዝብ ከኖረበት ቀየ እየተነቀለ ሜዳ

ላይ ሲጣል አይቶ ዝምታን አይመርጥም። አለምነው መኮነንና

ገዱ ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጥተው ደሃውን አማራ በሙሉ

ነፍጠኛ፤ ትምክህተኛ፤ ሌላም ሌላም እያሉ እያዋረዱ ፤ እየሰደቡ

ለሳዳቢ አሳላፈው የሰጡ የወያኔ አሽከሮች ናቸው። ለአማራ

ህዝብ የአያሌው በገዱ «መተካት» የተዋረደውን የአማራ ህዝብ

ክብር አይመልሰውም፤ ህዝቡ ያጣውን ነፃነት መልሶ

አያቀዳጀውም። ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠውን በአያቶቻችን ደምና

አጥንት የቆየውን መሬት አያስመልሰውም። የወልቃይት ህዝብ

የደም እንዳ እያነባ ለትግራይ በግዳጅ የተሰጠውን ለም መሬት

አያስመልሰውም። ታዲያ ስለምኑ ነው የአማራ ህዝብ የህወሀት

ብዓዴንን ልደት የሚያከብረው? በርሀብ ሲያልቅ ወያኔ

ስለደበቀለት? አማራው ክብሩና ታሪኩ ስለተዋረደ? አውሮፓና

አሜሪካ ስደት ላይ ያሉ ልጆቹ ውጡ በማይባሉበት ሁኔታ የርሱ

ግን ባገሩ ውጣ ተብሎ ስለተባረረና ሜዳ ላይ ስለተጣለ? የዘር

ማጥፋት ስለተካሄደበት? ለየትኛው ውለታው ነው የአማራ ህዝብ

የብዓዴንን ልደት የሚያከብረው? በአለም ላይ የመጨረሻ ድሀ

የተባለ ክልል ከአማራ ውጭ የት ይገኛል? አማራው ስደትን፣

ልመናንና እርዳታን እንደ አማራጭ እንዲከተል ስለተደረገ?

ነጻነቴን፣ አገሬን፣ ኢትዮጵያዊነቴን፣ ባንዲራዬን፣ በማለቱ

ስለተገደለ? ትምክህተኛ የደርግ ስርዓት ናፋቂ ተበሎ

ስለተሰደበ? የብዓዴን ልደት ከአማራ ህዝብ ጋር ምን

ያገናኘዋል? እንደ እውነቱ ከሆነ የአማራ ህዝብ ልደት

የሚሆነው ብዓዴን ሞቶ ተዝካሩ ሲወጣ ነው።

የህወሃት ስንቅና ትጥቁ የአማራ ጥላቻ መሆኑን ያለፈው የአምሳ

አመታ ታሪካቸው ያስረዳናል። ህወሃት «አማራ የትግራይ ህዝብ

ቀንደኛ ጠላት ነው» ብሎ የሚያምንና በዚህም መነሻ የታገለ

ቡድን ነው። ከዚህ ቡድን አማራው ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት

እንደማይገኝ መዘንጋት የለበትም። ይህንን በመገንዘብ የአማራ

ህዝብ ከህወሀት ብዓዴን ለመላቀቅ እንዳርበኝነቱ ዘመን

የነጻነትና ህልውናን የማቆየት ንቅናቄ መጀመር አለበት። ወያኔ

አንድ ሳሙኤልን ሲገድል አማራው መልሶ አንድ ወያኔ በመግደል

የወገኑን ደም ማፈስ አለበት። የአማራ ህዝብ ይህንን ካላደረገ

በህወሃት የተነጠቀውን ነፃነቱን፤በማን አለብኝነት የተቀማውን

መሬቱን፤ የተዋረደው ክብሩንና እየጠፋ ያለውን ማንነቱን በቀላሉ

ማስመለስ እንደማይችል መገንዘብ ይኖርበታል። ለነፃነትና

ለማንነት የሚከፈል መሥዋእትነት ደግሞ አስፈላጊ

መሥዋዕትነት ነው። የወያኔ ዘረኛ ቡድን ንጹሀንን እየገደለ፤

የህዝብን አንገት አስደፍቶ በማንነቱ ላይ እየተሳለቀ፤ ህዝብን

አጎሳቁሎና ረግጦ ሲገዛ በአይናቸው እያየንና በጆሯቸው እየሰሙ

ተንጋለው ለመተኛት ያልፈቀዱ የህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ሁሉ

የብአዴንን የመንፈስ አባት ወያኔን በሚችሉት በመዋጋት

ወገናቸውን ነጻ የማድረጉን ትግል በመጀመር አለባቸው፤

እየተገደሉ ዝም ብሎ መቀመጥን ከቀደሙት ኩሮዎች

አያቶቻችንና አባቶቻችን አልተማርንምና!

አሁን ካለንበት የመከራ ኑሮ ለመላቀቅ ብዙ መስዋዕትነትን

የሚጠይቅ ቢሆንም በአውሬው የወያኔ መረብ ውስጥ ሆኖ

የለውጥ ኃዋርያ ለመሆን መነሳት በራሱ በታሪክ የሚደነቅ ግዳጅ

ነው። እርግጥ ነው የለውጥ ኃዋሪያነት መሆን ትልቅ ሸከም

ያለው ነው። የለውጥ ኃዋርያነት የቤተ ዘመዳም ጥላቻን ወደ

ፍቅር ቀይሮ በጋራ ጠላት ላይ ማነጣጠር፤ ለእልህ አስጨራሽ

ትግል ራስን ማዘጋጀት፤ ከግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ትውልድን

አሻግሮ የማየት ራዕይን የሚጠይቅ ነው። ህወሃት አማራን

እያጠፋ ያለው ከፍቅር ይልቅ በጥላቻ ስለተሞላ፤ የታሪክን

ጉድለት በበቀል ለማስታገስ የሚመላለስ በመሆኑና ትውልድን

አሻግሮ ከማየት ይልቅ የስግብግብነት ስሜቱ ያየለበት ሆኖ

በመገኘቱ ነው። ይህንን የወያኔ የማይሽር ጥላቻ ዘግይተውም

ቢሆን የተገነዘቡ መንገዱ ሁሉ የተከረቸመባቸው ታጋዮች ወያኔ

በአማራ ላይ የመዘዘውን የበቀል ሠይፍ ለመመከት ራሳቸውን

በየግንባሩ አዘጋጅተው ህዝባቸውን ብቻ እየጠበቁ እንደሆነ

አውቃለሁ። አማራውም የሚሞትበትን የህወህት ብዓዴን ልደት

በያመቱ መደገሱን ወደ ጎን ትቶ ቆርጦ በመነሳት ለህልውናው

የሚበጀውን የትግል ሰይፍ አዘጋጅቶ እንደ አባቶቹ በመሳል

ከጠላቶቹ ሠይፍ በላይ የሾለ ሰይፍ በልቡ እንደመዘዘ ማሳየት

አለበት። ካሁን በኋላ ለአማራ ህዝብ ከወያኔ የሚከፋና የሚከረፋ

ጠላት ሊኖረው አይችልምና ይህንን ለዘረፋ የተሠለፈ፤ እኔ

ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል የሚልን የጥፋት ቡድን በመታደግ እኔ

ከሞትኩ ሠርዶ አይበቀል የሚለውን ሁሉ ነቅሎ ሥፍራውን

ለማስለቀቅ ሳያቅማማ በፅናት ለመታገል መነሳት ይኖርበታል።

ድል ለአማራ ህዝብ!

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.