ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት አለመቻላቸው ታወቀ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት አለመቻላቸው ታወቀ:-  ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን ብለው የተነሡ አካላትን አመጣጥ፣ ስልትና ምእመናን ሊወስዱት የሚገባውን መንፈሳዊና ሕጋዊ መፍትሔ በየቦታው በመረጃ አስደግፎ በማብራራት የሚታወቀው ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታኅሣሥ 26 ቀን 2008 ዓም ምሽት፣ ከማኅበረ ጽዮን የምሽት ጉባኤ ሲመለስ ባልታወቁ ሰዎች ተደበደበ፡፡

ደብዳቢዎቹ ዋና ዓላማቸው ጉዳት ማድረስ እንጂ ዝርፊያ እንዳልነበረ የገለጠው ዲያቆን ታደሰ፣ ሰዎቹ ይዞት የነበረውን ቦርሳ፣ ስልኩንም ሆነ ገንዘቡን ለመውሰድ ምንም ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ ከፊትና ከኋላ ሆነው በመደብደብ ወዳልታወቀ ሥፍራ ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉም በአካባቢው የድረሱልኝ ድምጹን ሰምተው በወጡ ነዋሪዎች ምክንያት ሊተርፍ ችሏል፡፡
የድብደባው ዓላማ ዲያቆን ታደሰን ይዞት ከተነሣው ዓላማ አስፈራርቶ ማስተሐቀር ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ገምተዋል፡፡

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.