ወያኔ 25 ዓመት ዘርፎ ያደኸየዉንና ያስራበዉን ህዝብ ለመደበቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ

ወያኔ 25 ዓመት ዘርፎ ያደኸየዉንና ያስራበዉን ህዝብ ለመደበቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ ። ኢትዮጵያን አብረው በሚመዘብሩ የዉጭ ሃይሎች መረጃና ፕሮፓጋንዳ በመታገዝ የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ እድገትና ብልግና ላይ እንድሚገኝ አርገው ሃላፊነት በጎደለው የዉሸት ፕሮፓጋንዳ መላዉን አለም ሲያታልሉ ቆይተው አሁን ገበናው እርሃብ እና እርዛት ብቻ ሆኖ በመገኘቱ ለህዝቡ ድህንነት ሳይሆን ለራሱ ስልጣንና ክብር በክፍተኛ ደረጃ በመቅበዝበዝ ተጨማሪ ወንጀል በመስራት ላይ እንድሚገኝ ታዉቆአል።

ወያኔ በተለይ በአማራው በኦሮሞው በአፋሩና በአኙዋክ ነገዶች ላይ ኣሰቃቂ የዘር ማጥፋትና የዘር ማውደም ወንጀል እስካሁን ድረስ እየፈጸመ የሚገኝ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ለማመን የሚያስቸግር የገንዘብ መጠን በተለያዩ የአሜሪካ የኤሮጳና የኤሺያ ባንኮች ዘርፎ ማካበቱ በየጊዜው ይዘገባል። እኤአ ከ2000 እስከ 2009 ብቻ 11.7 ቢልሊዮን የአመሪካ ዶላር መዘረፉን Global Financial Integrity (GIF) የሚባል ድርጂት አጋልጦአል።

በሌላ በኩል መለስ ዘናዊ ብቻዉን በግሉ አካዉንት 3.00 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አሽሽቶ በዉጭ ባንክ ዉስጥ መገኘቱን ሰሌብሪትይ ዶት ኮም ወብ ሳይት አጋልጦአል። ከታች ያለዉን ሊንክ ዪመልከቱ። በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከሰተው እርሃብ ካለፉት ጊዚያት የባሰ የሆነበት ምክንያት ወያኔ ሌሎችን አካባቢወች በነገድ በመከፋፈል በቀጥታ ለ 25 አመታት ዘረፋና ግድያ በማካሄዱ መሆኑን ኢትዮጵያዉያንና የዉጭ ሀገር መንግስታት ያዉቃሉ።

http://danilemulu.blogspot.co.uk/2015/11/blog-post_15.html?spref=fb

መለስ ዘናዊ ብቻዉን በግሉ አካዉንት ፫ ቢልሊየን የአሜሪካ ዶላር አሽሽቶ

መለስ ዜናዊ ብቻዉን በግሉ አካዉንት 3.00 ቢልሊየን የአሜሪካ ዶላር ዘፍፏል

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.