ዓማርኛና ግእዝ

አማርኛና ግእዝ ሲተያዩ ” አልፋው “አ” ተለውጦ “ሀ” የሆነበትን ምክንያት እንፅፋለን።

የዓለም ሁሉ ፊደል በአ ሲጀምር አልፋ አ የነበረው ጥንታዊው የኢትዮጵያ ፊደል ተለውጦ ሀ የተባለው በመካከል የሚገኘው ፊደል መጀመርያ እንዲሆን የወሰኑ ሊቃውንት ከአባ ሰላማ ጋር አብረው የነበሩ የአክሱምና የፅርዕ ሊቃውንት ሕፃናትን በማስተማር ጊዜ አ በሉ ከማለት ይልቅ ሀ በሉ ማለት ከውስጥ ያለውን የእስትንፋስ ሃይል ወደ ውጭ የሚስብ ስለሆነ ሀ የመጀመርያው ፊደል እንዲሆን በምስጢር አመዛዝነውታል ይባላል።

እስትንፋስ የሌለውን ፊደል አ መጀመርያ ከማድረግና አ ከማለት በፊት የእስትንፋስ ድምፅ ይቀድማል ብለው ሀ አሉ። ሁለተኛም አካላዊ ጠባይና አእምሮን የሚያንቀሳቅሱና የሚያፀኑ እስትንፋስና ነፍሳት ስለሆኑ ሀ የሚለው ድምፅ እስትንፋሳዊ ፊደል መጀመርያ እንዲሆን ወሰኑ። ሀ አፍ የሚያስከፍት ሐ የጉሮሮ ኀ የላንቃ ተብለዋል። ሀ ፣ ሐ እና ሀ ፊደሎች በግዕዝና በአማርኛ ግሶች ውስጥ ተወራራሽ ናቸው። የሚከተለውን አስተውል:

ግዕዝ አማርኛ
ሀለመ አለመ
ሀለበ አለበ
ሐረሰ አረሰ
ሐፀበ አጠበ
ሐልቀ አለቀ
ኀደረ አደረ 

በነገራችን ላይ ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ሊቃውንት በግዕዝ ሰዋሰው የፊደል ድምፆችን በአምስት አባሎች የሚከፍሏቸው ሲሆን እነሱም:
የጉሮሮ [ ሀ፣ሐ፣ኀ፣አ እና ዐ]
የትናጋ [ ቀ፣ከ፣የ እና ገ]
የምላስ [ ለ፣ረ፣ተ፣ነ፣ደ እና ጠ]
የከንፈር [ መ፣በ፣ወ፣ጰ፣ፈ እና ፐ]
የጥርስ [ ሠ፣ሰ፣ዘ፣ጸ እና ፀ] ናቸው።

ምንጭ: መፅሔተ ጥበብ
በሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ

‪#‎ራፋቶኤል‬

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.