የተሳሳቱ የአማርኛ አነጋገሮች

የተሳሳቱ የአማርኛ አነጋገሮች አዳማጭን ውዥንብር ዉስጥ ከመክተታቸዉም በላይ ተናጋሪዉ አማርኛ የመናገር ችግር እንዳለበትም ያመለክታሉ። አማርኛን በትክክል መናገር  መቻል ተናጋሪዉ ማለት የሚፈልገዉን ሃሳብ በትክክል ለማስተላለፍ ይረዳዋል። እኔ እዚህ ቦታ ነው ያለሁት ይባላል እንጂ እኔ እያልኩ ያለሁት ቢባል አለመግባባትን ይፈጥራል።

 ስህተት   ትክክል
እኔ የምለው ያለሁት  እኔ የምለው
እኔ እያልኩ ያለሁ እኔ ያልኩት
መጣሁኝ መጣሁ
ሄድኩኝ ሄድኩ
አልኩኝ አልኩ