የፍቅር ዘፈን ግጥሞች

የፍቅር ዘፈን ግጥሞች
Anaqech Kirar

የፍቅር ዘፈን ግጥሞች

መንደረኛዉ ሁሉ እሳት ጫሪ ነዉ
ያንን ገል አደራ ሰዉ እንዳይነካዉ

ምነዉ ብታስጠሪኝ እኔን አስታዉሰሽ
እደጅ ተቀምጨ እቤቴ ሳመሽ

ሐምሌና ነሃሴን እንዲያ ስዋትት
እንዴት በመስከረም ባበባ ልሙት

እንደምን አድርገሽ ትራመጃለሽ
የኛን ሐገር ኣልፈሽ ሳላይሽ ያደርሽ

እጁዋን ብጨብጠዉ እጄን አወዛዉ
እንደ መቀነቱዋ ዞሬ ዞሬ እዚያዉ

እንዴት ነሽ ኣይባል ሰዉ በሰዉ መካከል
ሳያት ዉዬ መጣሁ አይን አይከለከል

ሊማሊሞ ሆኖ ይታያል ተከዜ
ከማን ይስቅ ይሆን ፍቅሬ ይህን ጊዜ

ንስር በሮበሮ ይገባል ከዋሻ
የቆንጆዎች ሀገር እንዴት ነዉ ላምዋሻ

የላምዋሻን ሎሚ መሳይ ተረከዙዋ
አልነቀል አለኝ ከልቤ ላይ መርዙዋ

አትነካኩብኝ፡ያንን ልጂ በሞቴ
እንዲያዉም ዘንድሮ ሳሰቶአል ሰዉነቴ

ላምዋሻ አመድዋሻ አሰብል አስባት
እልቤ ላይ ቆማ ታነዳለች እሳት

አሳ አበላሻለሁ አባይ ዳር ነዉ ቤቴ
ዶሮ መረቅማ ከወዴት አባቴ

ዝናቡ ዘነበ ደጋ ደጋዉን
ጎርፍ ያመጣሽ እንድሁ ከዎንዙ ልቁም

አሙት ተረከዝሽን አንቺ ሳትሰሚ
ይመስላል እያሉ ትርንጎና ሎሚ

ሰምና ወርቅ አዝማሪና ማሲንቆ

ሰኞም ገበያ ነው እግር ላደረሰው
ቦሩም ገበያ ነው እግር ላደረሰው
ሁል ጊዜ ባንቻሮ እንዴት ይሞታል ሰው

እንደምን አርገሽ ነው ልቤን የረታሽው
ከቤቱ አሶጥተሸ ከደጅ ያሳደርሽው
ባለ ብዙ ዘዴ መለኛ ነሽና
መጥተሽ ቶሎ ዳብሽኝ ህመሜ ሳይጠና

 

ሌሎች ኣስደሳች የፍቅር ግጥሞችን ለማንበብ ይመዝገቡ

Leave a comment