መልከዓ ምድር

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮችና በሀይቆች የተሞላ ሲሆን፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይኅን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖራት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ የአየር-ንብረት በአምስት  ይከፈላል:-

  • የኢትዮጵያ ገጽታ ከህዋ በናሳ

    የኢትዮጵያ ገጽታ ከህዋ በናሳ

  • ዉርጭ ከባሕር ወለል  ከ3200 ሜትር በላይ የሚገኝ ቦታ እና  ማእከላዊ የሙቀት መጠኑ ከ16 ዲግሪ ሴ.ግ የሚያንስ፤
  • ደጋ  ከባሕር ወለል በላይ ከ2300 እስከ 3200 ሜትር የሚገኝ ቦታ እና  ማእከላዊ የሙቀት መጠናቸው 16 ዲግሪ ሴ.ግ የሚደርስ፤
  • ወይ ናደጋ  ከፍታቸው ከባሕር ወለል በላይ ከ1500 እስከ 2300 ሜትር፣ ማእከላዊ የሙቀት መጠናቸው ከ16 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 30 ዲግሪ ሴ.ግ የሚደርስ
  • ቆላ  ከባህር ወለል  በላይ ከ500 እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው እና የሙቀት መጠናቸውም ከ30 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 50 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርሱ አከባቢዎች ሲሆኑ
  • በረሃ ከባህር ወለል በላይ እስከ 500ሜትር እና ከዚያ በታች የሚገኙ ቦታዎች ሲሆኑ የሙቀት መጠናቸውም ከ50 ዲግረ ሴ.ግ ይበልጣል (ለምሳሌ ዳሎል)

ክረምተት (ዋናው የዝናብ ወቅት)  ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የበልግ ዝናብ በየካቲት መጋቢት እና በግንቦት ይጥላል። የቀሩት ወራት በአብዛኛው ጸሐያማ ናቸው።

ዋቢ መጻህፍት

ከፍዓለ ዓለሙ (1996) ጥጥ በሰሜን ኦሞ: :  ከገበሬውች ጋር የተደረገ ምርምር::  ፋርምአፍሪካ። ፋምፍሌት ቁጥር 12 (አዲስ አበባ)::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.