በብቸኝነትና አጽናኝ በሚጠፋበት ጊዜ

ሳዝን የሚያጥናና ስከፋ መካሪ
ምንም ወገን የለኝ ካላንድ ፈጣሪ

አቤት አምላኬ ሆይ የሰማይ አባቴ
ይታይህ የለሞይ በሰዉ መጠቃቴ

ድረስልኝ ስልህ ስምህን ጠርቼ
የምፈልገዉን አላቅም አጥቼ

አምላክ በጥበቡ የሰራዉን ቤት
ቢገፉት አወድቅም ቢነቀንቁት

በጣም ሰፋ በሎ ይስራ ቤታችን
ማዘኑም  እንድሆነ ሞልቱአል ከቤታችን

መጾሙን ይጾማል ሁሉም ያዳም ሊጅ
የሰአቱን ነገር የሚያውቅ የለም ኢንጅ

እሾክ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብሰው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው

ክበር ተመስገን የኛ ጌታ
ከጠዋት አንስቶ እስከማታ

ኑማ ኑማ ብለህ አታቸኩለን
እንመጣልሃለን ሌላም ቤት የለን
ከላይኛው መጠን ስራ ላንሰራልህ
በለመድነው ቦታ ብንቆይ ምን አልንህ

ጌታየ ግብርህን እንዳታሳንሰው
እምቢ ብሎ አይቀርም አንተ የጠራኸው

እዉነቱን ሳይጨብጥ ሙግት ያማረው ሰው
ዛሬ አለሁ አለሁ ቢል ነገ ለማፈር ነው

አምላኬ ብዬ ስጠራህ
ከድሃ ቤቴ ገብተህ
ልዉጣ አትበለኝ ቸኩለህ
ምናምን ብዬ ልሽኝህ

ከምድሩ ፈተና ከራብ ከስደቱ
እኛንስ የጎዳን ያለዘር መቅረቱ

ቤት እሰራ ብዬ ማሰሪያ ይዣለሁ
አንድማገር የለኝ በማዘን ቆሜአለሁ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.