ግጥሞች

የትውልድ እስትንፋስ

 

ምድር የሚታደስ ሀብት እያፈለቀ፣

ጥበብን በጥበብ አስሮ እያራቀቀ፣

ጭኖ እየመጠቀ በሀይድ ላይ ሀይድን፣

በትዉልድ እስትንፋስ ሲያመነጭ ሀሴትን፣

የትዉልድ ዉበቱ እያደር ሲፍካ፣

አለም ያለዉ እምቅ ገና መች ተነካ?

የትዉልድ እስትንፋስ ማሰሪያ ጉንጉኑ፣

ቅዳሴዉ ዉዳሴዉ የመኖር ዉጥኑ፣

ትዉልድ ከአብራኩ ትዉልድን አብቅሎ፣

ዘሩ እንዳይቀበር በራሄ ዘርዝሮ፣

ህዋዉን ይሞላል ትዉልድ ተሞሽሮ::

ህዋዉ እንዲቀደስ በትዉልድ አዝመራ፣

የትዉልድ እስትንፋስ ዘላልም ይጎምራ::

 

ሸንቁጥ አየለ: ጥቅምት/ 2005 ዓም

———————————————————————–

  • ባለአዕምሮ ጀግና
  • ጥበብና ፍቅር ሲይዝ ቅኔ ማህሌት ፣
  • ልብን ይማርካል የሚዳሰስ እምነት።
  • ሀብትም ሆነ ጉልበት  አላስታበለህም፣
  • ከፍታን ፍለጋ ለወገን ስትደክም፤
  • ፍቅር በመሸመን ለጥቅል ወገንህ፣
  • ከፍታን ሰብከሃል በግለ ዝቅታህ።
  • ከፍ በል ከፍ በል ብረር አንዳሞራ፣
  • ትልምህ ኮለል ብሎ በሰማያት ይጥራ።
  • የዝማሬ ድምጽህ ቢሆነን መረዋ፣
  • ነባቢ ነዉ ነብስህ ይዉጣ ወደ ህዋ።
  • ፈጣሪን አገኘዉ እኛን ወክልና፣
  • ጥበብና ሚስጥር እንሻለን እና።
  • ጥበብህ በፍቅር ታስሮ ተሸርቦ፣
  • የወገን ጥላ ነዉ ዘመንን ተሻግሮ።
  • ባላዕምሮ ጀግና የሚሰጥር ማህተም፣
  • ጥበብና ፈቅር ከትዉልድ ሲከትም።
  • ይፍለቅ ከማህጸን ባለአዕምሮ ጀግና፣
  • በዘመን ሂደት ዉስጥ የወገን ከፍታ ይታወጃልና።
  • ሸንቁጥ አየለ፤ ሚያዝያ 2003 ዓም፣ አአ:: ማስታወሻነቱ፤ ለባለ አዕምሮ ጀግኖችና ለወገን ለሚደክሙ ሁሉ

 

  • ይሙት እንጅ ጀግና
  • ትዉልድ በከፍታ በህዋ እንዲበር፣
  • የሰዉ ሰዉነቱ ጭብጡ እንዲከበር፣
  • ይሙት እንጅ ጅግና ለወገን ከፍታ፣
  • እሽሩሩ በሉት ከፍኑት በበፍታ::
  • አትሙት አትበሉት እንቅፋት ሆናችሁ፣
  • ምቱለት እስክስታ ጀግናዬ እያላችሁ::
  • ፈሪማ ከብት ነዉ ይልሳል አተላ፣
  • ቁምነገሩ ለሱ ማደሩ እየብላ፣
  • እንኩዋን ለወገኑ ለቄንሳዉ የለዉም የክብር አለላ::
  • ጀግና ከሌለበት አይጣፍጥም አገር ገበያምአይደራ፣
  • ፈሪማ አልጫ ነዉ ወጥ እንኩዋን አይሰራ::
  • እዉቀት ሲተነተን በጥበብ በጸና፣
  • ፍትህም ሲመዘን በልቦና ቃና፣
  • የጀግና ፍሬ ነው መልካም ነገር ሁላ፣
  • ገለባው የፈሪ ዕራዕይዉ ነጠላ::
  • ≈      =      ≈

 

  • ፖለቲከኛ
  • አንት ፖለቲከኛ፣
  • ዜጋ ነኝ ስማኛ::
  • ብዬ ብጠይቀዉ ፖልቲከኛዉን፣
  • እኔን ተውኝና ሊሳደብ ጀመር መሰል ጉዋደኛዉን::
  • ዜጋን እናስቀድም ብለው ተማምለዉ፣
  • ቃላት በቃላት ላይ በፍጥነት ደርድረዉ፣
  • በፍጥነት ተጣሉ፣
  • አርማቸዉን ጣሉ፣
  • ደግሞ ምን አገባህ አንተን ባገር ጉዳይ፣
  • አገሩ የእኔ ነው ከምድር እስከ ሰማይ፣
  • እኔ እመራዋለሁ አዋቂ የታለ ደግሞስ ከእኔ በላይ፣
  • አንተ ተከታይ ነህ – ለመሪነት እማ አንተ የካብ እንቡዋይ፣
  • መቼም ባህል ሆኖ ተደናቁሮ ኑሮ፣
  • ይጀምራል ወገን ጅራፍ በመማዘዝ ሊቀፍል ለኑሮ፣
  • ቢሆን ለተልእኮ አርማዋ የአገር፣
  • አገር የጋራ ነዉ ይሉንስ አልነበር፣
  • አብሮነታቸዉስ ይሰምር አልነበር::

 

  • ———————— 
  • እኛም ቅኔ ልንሆን 
  • ቅኔ ነች ሀገሬ – ትውልድና ስሬ ፣  ሰሙን እቆጥርና ቅኔዉን ጀምሬ፣ መዉጣት ያቅተኛል-በሀሳብ መጥቄ ፣  ደሜን አንጠርጥሬ አጥንቴን ሰንጥቄ፣ ዉሉን አላዉቀዉም በተግባር አርቅቄ::  የአዳም ስሩ ነሽ- የልጆቹ መንደር፣ የትዉልድ መፍለቂያ የአንድነት ድዉር፣  መንደርደሪያ ቀዬ – ዉህድ አምባ ምተር::  ሐመር የፍጥረቱ መፍለቂያ ዉበቱ፣ ምንጭነሽ የአዳም -መታሰሪያ እትብቱ፣ ቅኔነሽ ዝም ብሎ – ሙዳዬ ሙስጥሩን፣ ቁልፉን አንስተናል እኛም ቅኔ ልንሆን::  ————————————- ሸንቁጥ አየለ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.