ሽለላ

ስለ ፉከራ እና ሽለላ መንደርደሪያ

ኢትዮጵያዉያን አማሮች የታሪክ የባህል እና የስነጽሁፍ ባለጸጋዎች ናቸው። የተቀደሰዉን የግእዝ ቁንቁአቸዉን ለጸሎትና እግዚአብሄርን ለማመስገን ሲጠቀሙበት ዓማርኛን ደግም ለአስተዳደር ለአለማዊ ንግግሮች  ጽሁፎች ለወታደራዊ ስርአት ልቦናቸዉን ለማነቃቃትና ለመራቀቅ ይጠቀሙበታል።  ፉከራ ሽለላ እና እንጉርጉሮ  ከጥንት ጀምሮ መንፈሳቸዉን ለማረጋጋትና ለማጠንከር የሚጠቀሙበት ለሸላዩና ለፎካሪዉ ብቻ ሳይሆን ለሚያዳምጠውና ለሚያየው ሰው ክፍተኛ የሆነ መነቃቃትን ድፍረትንና አስተዋይነትንም ጭምር የሚፈጥር ነው።

ከአድዋ ጦርነት በፊትም ሆነ በሁዋላ ፉከራና ሽለላ ተዋጊዉን በማበረታታት በማስተማርና በማጽናት የኢትዮጵያ ህዝብ በነጻነት እንዲኖር የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ አድርገዋል። ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ይህንን ጠቃሚ ባህላችንን በወጉ መጠበቅና ማሳደግ ይኖርብናል። የጸረ ኢትዮጵያዉያን አላማ የአማራን ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ የጥቁር አፍሪካዉያንንም ታሪክ ማጥፋት ስለሆነ ሸለላን እና ፉከራንም ክብራቸዉን ለመንካት ሲዉተረተሩ ቀንዳቸዉን በማለት ማሳፈሩ ተገቢ ነው። መልካም የንባብ ግዜ ይሁንላችሁ::

ደህና ጎበዝና አንበሳ አንድ ናቸው
ደህና ጎበዝና ነብር አንድ ናቸው
ማንንም አይነኩ ካልደረሱባቸው

ንዳዉ ላሙን አቡአራው ይነሳ
ይመጣ የለም ኮርማው እያገሳ

አባቱ መሬት ላይ የተኛዉን በሬ
ቆስቁሰው ቆስቁሰው አደረጉት ኣዉሬ

ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው
ኣስቀድሞ መግደል ኣሾክሻኪዉን ነው

አትመነው የባንዳን መብለጭለጭ የባንዳን ጎፈሬ
እንኩአን በክላሽን ይሸሻል በወሬ

የፍየል ወጠጤ ትከሻው ያበጠ ልቡ ያበጠበት
እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት
የማትረባ ፍየል ዘጥኝ ትወልዳለች
ልጆቹዋም ያልቃሉ እሱዋም ትሞታለች

ተልባ ጠጣሁ እና የተበጠበጠ
አላስቀምጥ አለኝ ሆድ እየቆረጠ !!

እልም ካለው ጫካ እልም ካለው ዱር
ሲነጋገር ያድራል ከመውዜሩ ጋር

አዳባይ ዥረት ያለሽ አሞራ
ስጋዉን በልተሽ ለምዱን አደራ

ሀገራችን ወሎ ወንዛችን ተከዜ
ማነው የሚደፍረን በተቆጣን ጊዜ

ፋኖ ደስ ይለናል ሲታጠቅ ማለዳ
የሚያበላ መስሎ የሚሀኝ እንግዳ

እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

አምናንም አለፍኩት እንዳይሆን እንዳይሆን
ካቻምናን አለፍኩት እንድይሆን እንዳይሆን
ደሞ ክራሞተ ዘንሮ እንዴት ይሆን።

እረ ጎራው እረ ጎራው!

እንግዲህ ጣይ ለጣይ ከሆነ መንገዱ፣
ጥላ ጥላ መርጦ ይበጃል መሄዱ!!

እረ ጎራው ናለኝ (2)

እኖር ብሎ ከሰው እድር ብሎ ከሰው
የአንበሳን ትክሻ ከብት ተንተራሰው!!
እረ ጎራው(2)

አለኝ ክፉ በሬ እንደኔ የከፋው
ሳሩን ብደብቀው ጭዱን ባፉ ተፋው!!

ፈትየለት ነበር ላንድ ወዳጄ ሸማ
ምን አደርገዋለሁ ሐሩ ከጠፋማ!!

አርሶ መራብና ተኩሶ መሳት፣
እያደር ይፋጃል እንደገል እሳት።

አረ ጎራው አረ ጎራው

ተንኮለኛው ገደል ዝንጀሮ ይጠልፋል በሬ ያሳልፋል!
ሞኝ ያመጣው ነገር ለሁሉም ይተርፋል።

እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ
እዚህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ወይ አለው
ጎበዝ ተነቃነቅ ይህ ነገር የኛ ነው።

ልቻል ማለት ልለፍ ማለት ካስነካብኝ ስሜን
ልቻል ማለት ልለፍ ማለት ካስነካብኝ ክብሬን
ሂጄ ልከፈልለት አጥንትና ደሜን

ይመከራል ይረዳል ብየ እንጅ
ድሮስ ምን ዋጋ አለው የጠላት ወዳጅ

እንግደኢህ ሸለቆው ቁዋጥኙም ይደማል
በማን ጊዜ ጠላት ሃገርን ያስማማል

ዘነበች ታዴና ሞላ ሰጥ አርጌ

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.