የኢትዮጵያ ታሪክ ከኦሪት (ዘመነፍዳ) እስከ ዘመነ ምህረት (ዓመተ ምህረት)

የኢትዮጵያ ታሪክ ከኦሪት (ዘመነፍዳ) እስከ ዘመነ ምህረት (ዓመተ ምህረት)

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፡ መሠረት እና ጥንታዊነት!

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መሠረቱና ጥንታዊነቱ፡ ከፍጥረት ልደት፡ ማለትም፡ እግዚአብሔር፡ በሥነ ፍጥረት ካስገኘው ቀስተ ደመና ነው፤ ይህውም፡ ከአዳምና ሔዋን አንሥቶ፡ ፲ኛ ትውልድ በኾነው፡ በኢትዮጵያዊው ጻድቍ ኖኅ፡ ልኡክነትና የቃል ኪዳን ተዋዋይነት የተገኘ ነው።

በኪዳነ ልቦናው የመጀመሪያውና በኪዳነ ኦሪቱ የመካከለኛው አዝማናት፡ ይህ፡ የቀስተ ደመና ሰንደቅ፡ ከኖኅ ሲወርድ ሲዋረድ ቆይቶ፡ የዮቶር፡ የልጅ ልጅ በኾነው፡ በኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ ሢመት በነገሠው፡ ”አጼ ሰንደቅ” አማካይነት፡ የአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ቀለማት ምልክቶቹ፡ በሸማና በዘንግ ተወጥረው፡ አገልግሎታቸውን በግዘፍ ቀጥለዋል።

በኪዳነ ምሕረቱ የመጨረሻው ዘመን፡ ”ሞአ አንበሳ፡ ዘእምነገደ ይሁዳ” ማለትም፡ ”ከይሁዳ ነገድ የኾነው አንበሳ፡ ድል ነሣ”የሚለው፡ ለኢትዮጵያዊዉ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረው መለኮታዊ ቃል፡ ትእምርተ መስቀልን በያዘ፣ የንግስና ዘውድን በደፋና በግርማ መፍርህ በተጠረረ አንበሳ፣ እንዲሁም፡ ”ኢትዮጵያ፡ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር” ማለትም፡ ”ኢትዮጵያ፡ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች” ተብሎ፡ በሴት አንቀጽ፡ ለድንግል ማርያም የተነገረውን መዝሙራዊና ትንቢታዊ ቃል፡ በሥዕላዊ መልኵ፡ በዓላማቸው ላይ በማተምና በመቅረጽ፡ ማውለብለቡን ቀጥለዋል።

ይህ፡ የአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ምልክት፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያትን፡ እያንዳንዳቸውን በተናጠልና መንግሥታቸውን በጋራ፡ ከሰይጣናቱ እና ከክፉ ሰዎች ጠላትነት ጠብቆና ተከላክሎ፡ ከጥንታዊ እና ቀዳማዊ ማንነታቸው ጋር፡ ይህው ከዓለሙ ሀገራት ኹሉ ተለይተው፡ በዚህ እውነተኛ ማንነታቸው ለ፯ሺ፶፻፯ ዓመታት፡ በሕያውነትና በዘለዓለማዊነት እንዲቀጥሉ ያስቻለ፡ መለኮታዊ ጋሻ ነው። (ዮሓ. ራእ. ምዕ. ፬፥ ቍ. ፫።)

ዛሬም፡ በዚህ፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚያምኑትን ኪዳናውያንና ኪዳናውያት፡ የቀስተ ደመና ምልክቱ፡ አማናዊና እውነተኛ መገለጫዎች የኾኑት፡ ኢየሱስ ክርስቶስና ድንግል ማርያም በመኾናቸው፡ በዚሁ ቃል ኪዳን አማካይነት፡ በማንኛው በኵል ለሚቃጡና ለሚነሡ ጥቃቶች፤ ለምሳሌ፡ ዓለሙን እያስጨነቁ ካሉት፡ የአሸባሪነት እና ገዳይ ከኾነው የ”Ebola” ተውሳክ፡ ነጻ ናቸው።

ይህን መለኮታዊ ትእምርት (ምልክት)፡ ዓለሙ ኹሉ ተቀብሎት እየሠራበትና እየተጠቀመበት እንዳለ፡ ይህው ይታያል፤ ለምሳሌ፡ በየመንገዱና በየዐደባባዩ ላይ፡ የተሽከርካሪ ፍሰትን ለመቆጣጠር፡ ዓለሙ እየተጠቀመበት ያለው፡ የመተላለፊያ መብራት (Traffic Light) አደጋን በማስቆምና በመከላከል ፍቱን መሣሪያነቱ የተረጋገጠለት ነው። 

ኪዳናውያንንና ኪዳናውያትን፡ ከማናቸውም አደጋ ጠብቆ ያለው፡ ይህ፡ የቀስተ ደመና ምልክት፡ ”በግንባራችን ላይ፡ በመለኮት እጅ የታተመ በመኾኑ ነው!”። ባለራእዩም፡ ”የእግዚአብሔርም ማኅተም፡ በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር፡ በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም፣ ወይም፡ ማናቸውንም የለመለመ ነገር፣ ወይም፡ ማናቸውንም ዛፍ፡ እንዳይጐዱ ተባለላቸው!” ያለው፡ ይህንኑ ያረጋግጣል። (ዮሓ. ራእ. ምዕ. ፱፥ ቍ. ፬።)

በመጨረሻም፡ እኛ የምንቀበለው፡ እውነተኛው ሰንደቅ ዓላማችን፡ ይህ፡ ከታች የተመለከተው ነው። ነገር ግን፡ ይህ፡ ሰንደቅ ዓላማ፡ በግዘፋዊና በሥዕላዊ መልኩ፡ እንዲህ መቅረቡ፡ ዓለሙ እንዲያየው በሚል እንጂ፡ ለአምልኳችን የምንጠቀመው አለመኾኑን፡ በተገቢው ማወቅ ይኖርብናል። እኛ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ በእውነትና በመንፈስ ቅዱስ አምልኳችን፡ ግዘፋዊ የኾነ ማንኛውም፡ መስቀልን ጨምሮ፡ ምልክትና ዓርማ አያስፈልጉንም።

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.