የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሰረት

የኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር መሰረቱ ቅዱሳት መጻህፍት ናቸው

የኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር መሰረቱ ቅዱሳት መፅሐፍትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አባቶች ያስተምራሉ። ከነዚህ መፅሐፍት መካከል መፅሐፈ ሔኖክ አንዱ ሲሆን ለአቡሻህር መፅሐፍ መዘጋጀት ምክንያት ሆኗል።

የኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር መፅሐፈ ፀሐይ እና መፅሐፈ ብርሃን

በቅርብ ያገኘነው ማስረጃ እንደሚያስረግጠው ታዲያ ከመፅሐፈ ሔኖክ ባሻገር ኢትዮጵያውያን የራሳቸው የዘመን አቆጣጠር እንዲኖራቸው ከረዷቸው መፅሐፍት መካከል መፅሐፈ ፀሐይ እና መፅሐፈ ብርሃንም በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ መፅሐፍት አጠቃላይ የስነ ሕዋንና፣ የፀሐይ ፣ የጨረቃን እንዲሁም የከዋክብትን እንቅስቃሴ ባህሪ በሰፊው ስለሚተነትኑ ነው።

በየትኛው መድረክ የኢትዮጵያውያን የዘመን ስሌት ጥበብ ሲነሳ እነዚህ ሶስት መፃሕፍት ተያይዘው መነሳት አለባቸውና ሊቃውንቱም ሆኑ አገራዊ ሚዲያዎች ትኩረት ሊያደርጉባቸው ይገባል። 

እንኳን አደረሳችሁ።

ራፋቶኤል

እንቁጣጣሽ (የኢትዮጵያ አዲስ ዘመን መግቢያ) ስርአትን ወግንና ባህልን በተከተለ መንገድ በታላላቆች ምረቃ ሲከበር። አቅራቢ ያራዳ ሙዚቃ።

የአማርኛ የወራት ስያሜና የግእዝ ስረወ ቃሉ

ለተጨማሪ መረጃ መገናኛዉን ይከተሉ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.