Skip to content
አማርኛን መናገር መቻል አንዳንድ ቀላል የሚመስሉን ነገሮች ጭምር ለማስረዳት ይረዳናል:: ያ ሳይሆን ቀርቶ ግልጽ ሆነው ትርጉም ካላገኙ በጽሁፍም ሆነ በቃል የምናደርገዉን የሃሳብ ልዉዉጥ ከማወካቸዉም በላይ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባትን በመፍጠር ችግር ላይ ሊጥሉን ይችላሉ:: አንዳንዶቻችንም “እኛ ኢትዮጵያዉያን ይህን ማድረግ ነበረብን ግን አናደርግም” በማለት በቁጪት እራሳችንን እንወቅሳለን:: አልፎ አልፎም ተሳስተን ሌላዉን እናሳስታለን :: እርግጥ ነዉ ብዙ የማናዉቃቸዉና የምናዉቃቸዉ ነገሮች ስላሉ መማር አለብን:: እድገት ማለት ደግሞ እነዚህን ትንንሽ ነገሮችን እያስተካከሉና እየገነቡ በቀጣይነት መጓዝ ነው::
ልብ ብለው በንግግር ወቅት ካዳመጡ የግለሰቦችን የመናገር (የቋንቋ) ችሎታ ሊረዱ ይችላሉ ሀሳባቸዉን በቀጥታ መግልጽ የሚችሉ ሰወች ብቻ ናቸው። በመሆኑም ስንነጋገር የምንጠቀምባቸው ቃላት፤ ኣገባባቸዉ ማለትም ቅደም ተከተላቸዉ (logical Sequences) ኢንዲሁም የቃሉ ትክክልኛነት ኣድማጪን ከመሳቡም በላይ ተናጋሪዉ መልእክቱን በሚገባ ያስተላልፋል። ከዚያም አልፎ የአንድ ሰው የኣነጋገር ስርአትና ባህርዩ (Personality) ስሚንጸባረቅ ሊያስከብረዉና ታማኝ ሊያደርገዉ ይችላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ኣደናጋሪ ወይም የተሳሳቱ ኣባባሎች ሳይገጥሙን ኣይቀሩም።
የዛሬዉ የእዉቀት መቋደሻ ርእስ:- ለመሆኑ “እኔ እያልኩ ያለሁት ይባላል እንዴ?” ሃሳብዎትን (እዉቀትዎትን) ያካፍሉን::