አባባሎች በግጥም

ዘመድ ከዘመዱ

አህያ ከአመዱ

ከድጡ

ወደ ማጡ

ላም አለኝ በሰማይ

ወተቷንም አላይ

ሰው ሲያማ

ለኔ ብለህ ስማ

ወደሽ ከተደፋሽ

ቢረግጡሽ አይከፋሽ

ባጎረስኩ

እጄን ተነከስኩ

ሳል ይዞ ስርቆት

ቂም ይዞ ፀሎት

ላያዘልቅ ፀሎት

ለቅስፈት

ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ

አብረህ ተወቀጥ

ያልጠረጠረ

ተመነጠረ

ስራ ለሰሪው

እሾህ ለአጣሪው

አባቱ ዳኛ

ልጁ ቀማኛ

ተልባ ቢንጫጫ

በአንድ ሙቀጫ

አትሩጥ

አንጋጥ

መቀመጥ

መቆመጥ

ካለ ፈጣሪ

አሟጠሽ ጋግሪ

የትም ፍጪው

ዱቄቱን አምጪው

ፍየል ከመድረሷ

ቅጠል መበጠሷ

አለባብሰው ቢያርሱ

በአረም ይመለሱ

ንገረው ንገረው

እምቢ ካለ መከራ ይምከረው

ከስስታም አንድ ——

ዶሮን ሲያታልሏት

በመጫኛ ጣሏት

የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ

አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ

ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ

ይበጣጠስ

አተርፍ ባይ

አጉዳይ

ድር ቢያብር

አንበሳ ያስር

አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል

የሰዉ ፈላጊ የራሱን ያጣል

ሳያረጋግጡ ወሬ

ሳይገድሉ ጎፈሬ

ሰው ሲያማ

ለኔ ብለህ ስማ

ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ

ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም 

ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው 

አዛኝ ቅቤ አንጎች 

እርስዎ የሚያዉቁቅ ምሳሌአዊ አነጋገር ካለ ከታች ባለዉ ቦታ ዉስጥ ቢጽፉልን ይደርስናል::

ወደ እራስጌ ለመመለስ ይህን ይጠቁሙ

ወደ ዓማርኛ ለዛ ለመመለስ ይህን ይጠቁሙ

 

Pages: 1 2

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.