ሰምና ወርቅ

ሰምና ወርቅ

♣ሰምና ወርቁን ለማወቅ ከግጥሙ ላይ ይጫኑ (ይጠቁሙ)

ነይልኝ በፈረስ በሚገስግሰዉ!
መቸ በቅሎ ያዉቃል እንዳንቺ ያለ ሰዉ

ሞጣ ቀራኒዮ   ምነዉ አይታረስ
በሬ ሳላይ መጣሁ ዚያ እስከዚህ ድረሰ

አዉው ብትል ጅቦ መች እፈራሃለሁ
ና ብላኝ ና ብላኝ እደጅዋ ቆሜአለሁ

አዳራሹ ሰፊ ቤቱ አልጠበባችሁ
በተራ በተራ ምነዉ መግባታችሁ?

ከበጌምድር ጎጃም ተሻገር ያልከኝ
ሰሜን ወደሁዋላ ተመልከትልኝ

ለምን ገለበጡት ወተቱን በጋን
ችዬ እገፋዋለሁ የማልለዉን

ከዚያ ላይ ያለች፣ሸክላ ሰሪ፣
ድሃ ናት አሉ፣ ጦም አዳሪ፣
ማን በነገራት፣ጥበቡን፣
ገላፈር መሆኑን።

በጎጃም ያካፋል በሸዋ ፀሀይ 
በጎንደር ደመና መቅረቱ ነውይ 

ቤተስኪያን ስሞ፣ ለመኖር፣
መልካም ነው አሉ፣ ጎንደር፣
አይቀርምና፣መዳኘት፣
ከተማሰው፣ መግባት።

በገዛ አገራችን በገዛ ወንዛችን 
በሉ እጠቡንና እንግባ እቤታችን

ቢወጡም ቢወርዱም ቢዞሩም በዓለም፣
እንደ ባልንጀራ የሚስማማ የለም
 

ቢጮኸው ቢያነባው ስላልጠቀመው፣
ድኾ በጉልበቱ ነው ያለቀሰው
 

ባለሁበት ሰፈር፣
እኔን ጠበበኝ ምድር፣
አንተ ነህና አለኝታዬ፣
አስፋ ወሰን ጌታዬ
 

ባልሻሪው ቢሠራ በዶማ ባካፋ፣
የዘሩትም ቀረ አልበቀለም ጠፋ
 

ባልሽ ወዴት ሄደ ብለን ብንጠይቃት ስለ ጉዳያችን፣
ተሰብሮ አሁን መጥቶ ተኝቷል አለችን
 

ቢገዛን በጠላሁ የራስ ኃይሉ ልጅ፣
የኃላውን ካሳ ብፈራ ነው እንጅ
 

ባሁኑ ጦርነት ማንም ማን አይኮራ፣
ኃይለ ሥላሴ ነው ይኸንን የሠራ
 

ይቀጥላል

Pages: 1 2 3

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.